2016 ኦክቶበር 21, ዓርብ

ኤርትራ #ERITREA

ኣኬልዳማ Vs ኤርትራ
30
ብር Vs 30000ብር (ይሁዳ Vs ኣፄ ምንሊክ)
2 ይሁዳዎች ልዩነትና ኣንድነት!
ጌታን 30 ብር የሸጠው ይሁዳና ኤርትራን 30000ብር የሸጠው ኣፄ ምንሊክ ሲነፃፀሩ።
ፈጣሪን 30 መሸጥና ኤርትራን 30000 ብር መሸጥ በጣም የሚለያዩ ነገር! ቢሆኑም የሚያገናኙዋቸው ነጥቦችና ጌታን የሸጠው ይሁዳ ኤርትራን ከሸጠው ጋሽ ሚኒሊክ የሚሻልበት ጉዳዮቹም ኣሉ።
የመመሳሰላቸው ነጥቦች፦
1.
ሻጮቹ የፈጣሪን ፍጡራን መሆናቸው፣
2.
ሁለቱም ከሃዲ መሆናቸው፣
3.
ይሁዳ ፈጣሪውን የሸጠበት ብር ሃገር ከሸጠው በጣም ቢያንስም በግብይቱ ሰላሳ የሚለው ቃል ያገናቸዋል፡፡ እንዲህ የጊዜና የዋጋ ንረት ታሳቢ ካደረ ግን ጥንት ጌታ የተሸጠበት 30 ብር ኤርትራ ከተሸጥበት 30000 ብር ሲነፃፀር ቢበዛ ወይም እኩል ቢሆን እንጂ ኣያንስም።
4.
የገዥዎቹ መመሳሰልና የግዥያቸው ውጤት፡
ይሁዳ ተፀፅቶ ኣዝኖ 30 ብሩን ለገዢዎቹ ጥሎላቸው ነበር እነሱም ብሩን ኣንስተው መሬት ገዙቡት ይህ መሬት የተረገመ የደም መሬት ኣኬልዳማ ይባላል። ኣሁንም 30000 ጣልያን የገዛት ኤርትራም የደም መሬት ከመሆን ኣልዳነችም።
***የልዩነታቸው ማሳያና ጌታ የሸጠው ይሁዳ ሃገር ከሸጠው የሚበልጥበት ነጥብ።
. ይሁዳ ኣፄ ምንሊክ የሚሻልበት ነጥብ ጌታዉን መክዳቱና መሸጡ ፀፅቶት የተቀበለውን ብር ጥሎ ራሱን ማጥፋቱ፡ ኣፄ ምንሊክና ተከታዮቻቾው ግን ከዚሁ በተቃራኒ መሬት መሸጣቸው ህዝብን መክዳታቾው ዘንግተው በሃጥያታቾው ገሃነም ሌላውን ንፁሁን ለመቀቀል ለዘመናት ጥረት እየዳከሩ ነው። ሓጥያታቸው እንደ ጀብድና ፅድቅ ነው የሚቆጥሩት።
ታህሳስ 29 1891 / ከቺኮዲላ ለማርቲኒ የተላከው ቴሌግራም
ከህዳር 1891 / ጀምሮ ትግራይ ላይ ሰድሮ የነበረው የራስ መኮነን ጦር የምግብ እጥረት ስለ ገጠመው ዘርፎ እንዳይበላ ህዝቡን እንዳያሸፍት ስጋት ስለኣደረ ይህንኑ በመግለፅ ከኣፄ ምንሊክ ህዳር 14/1891 በተፃፈው ደብዳቤ መሰረት ከኢጣልያ 30000 ብር ብድር ተስጥቶ የራስ መኮነን ጦር ከኤርትራ ምግብ እንዲገዛ ከተደረገ በምትኩ በክርክር የነበሩት ኣውራጃዎች በጊዝያውነት ሳይሆን በዘለቄታዊ ለኢጣልያ መንግስት ለመስጠት ኣፄው ዝግጁ መሆናቸው የሚገልፅ ነበር።
ኣከታትለው ደግሞ ኣፄ ምንሊክ ምንም ካሳ ሳይጠይቁ ከያዝናቸው መሬቶች አሁን ኤርትራ በመባል ከምትታወቀው ሠራየ በሙሉና ኣከለጉዛይ በሙሉ ከለጎና ሺምዛና በቀር ለመስጠት ፈቃደኛ ናቸው የሚል መልእክት የካቲት 1 ቀን 1884 / ለማርቲንና ለሮማ ተላለፈ። ምንጭ (የኢትዮጵያና የኤርትራ ግጭት መንስኤ እና መፍትሄ በዶ/ ደጀ. ዘውዴ ገፅ 30.)
በዚህም ይህ ተወደደም ተጠላም ተብሎ በታሪክ ሲመፃደቅለትና ሲዘመርለት እንዲሁም ሲወደስ የነበረውን ሚኒሊክ በአንድ ግዜ በኔው ምልከታ ዘጭ የታሪክ አተላ ነው አልኩት፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ