ለትዝብት ነው እንጂ...! የሽዋየዎችና የኣሞራዎች...ታሪክ ማንበብ 0!
በእርግጥ ለሽዋየዎችና ኣሞራዎች የኣፄ ዮሃንስ ጥሩ ተግባር ሁሌም እንቆቅልሽ ... እንደሆነ ባልዘነጋም .. ለትዝብት ግን
"በኣፄ ቴድሮስ ዘመን የእንግሊዝ ወታደር በፍጥነት ከኢትዮጵያ መውጣት፡ ለኢትዮጵያውያን ሙሁራን እንቆቅልሽ! ነው" ይለናል ሊቃቸው በቅርቡ የሞተው ፕሮ. ባህሩ ዘውዴ።
"ለትዝብቱ ነው እንጂ ጭቡየ ቢጎዳም ኣይገድልም!" እንደሚባለው ኣሁንም የነሽዋየና ኣሞራው ወሬና ፅሑፍ ባይጠቅምም.. እንታዘባቾውና.
የእንግሊዝ ጦር መሪ ሳይውል ሳያድር ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ኣፄ ዮሃንስ ከናፒየር መስማማቱ ራሱ እየገለፀ በተቃራኒው ደግሞ ይህ ጉዳይ ራሱ መልሶ እንቆቁልሽ ሁኖዋል ይለናል!
"የእንግሊዝ ሰራዊት መሪ የነበረው፡ ጀኔራል ናፕየር በኣፄ ቴድሮስ የታሰሩበትን ዜጎች ኣስፈትቶ ሳይውል ሳያድር! ኢትዮጵያ ለቆ እንደሚወጣ፡
የንጉሱ ዋና ተቀናቃኝ ከነበረው በዝብዝ ካሳ
(ኣፄ ዮሃንስ) ስምምነት ላይ ደርሰዋል!!"
በዚህ መሰረትም የእንግሊዝ ጦር ከኣገር ወጣ!
ነገር ግን ባህሩ ዘውዴ በፃፈው የኢትዮጵያ ታሪክ ከ 1847 – 1993 ሳይቀር የእንግሊዞች በፍጥነት ከኢትዮጵያ መውጣት ለኢትዮጵያውያን ሙሁራን እንቆቅልሽ! እንደሆነ ይገልፀዋል!
ነገር ግን ምኑ ላይ ነው እንቆቅልሽ? በስምምነት የተደገፈና ግልፅ በሆነ ጉዳይ እንቆቅልሽ ምን ኣመጣው?
በቃ ይህ መከረኛ የጎጠኝነትና የቋንቋ ኣስተሳሰብ ያመጣው እንጂ ሁሉም ነገር ግልፅ ነው።
እንድያዉም እንቆቅልሽ መሆን የነበረበት
ዜጎችን በመግደልም ይሁን በባዶ ስሜት ተራ የውጭ ኣገር ዜጎችን በማሰር ሃያልዋ ኣገር እንግሊዝ ጋር የተጣላውና በጊዜው ህዝቡና ወታደሩ የከዱትና የጠሉት የንጉሱ የኣፄ ቴድሮስ ቂላቂል ተግባር በተቃራኒው ጀግናና ኣርቆ ኣሳቢ በማለት የሚያወድሱበትና የሚፎኩርበት መነሻው እውነት ነው።
በዚህም ይሁን በዚህ ብዙ የአገሬ ታሪክ ላይ እኚህ እድሉ አግኝተው በጎጥ ያማከለ የታሪክ
አፃፃፍ ማዕከል አድርገው የሚፅፉ ወይም የመጨረሻ ዳራቸው ከዚሁ የጎጥ በሽታ እንዳይወጡና ለሆዳቸው ብቻ የሚያድሩ በሂወት የሌሉ
የታሪክ ፀሐፊው ብሎም እነ አለሁ ባዩ ፕሮ. መስፍን ወልደማርያምን ጨምሮ በጥቁር ታሪክ አፃፃፍ ስታይል የሚታወቁ የጥቁር ካፖርት
ለባሾች ናቸው፡፡ ያቅማቸውነ ያህል ግን በጣም ብዙ በሚባል አኩሃን ታሪክን አጨማለቋት፡፡ አሁንም የነሱ ትላትል በጣም ብዙ ናቸው፡፡
እንደ ሚሞሪ ካርድ ያገኘውን ሶፈትዌር የሚቀበል ትውልድ አለመሆናችን ማሳየት ነው የሚበጀው ዋ…ዋ… ጠንቀቅ፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ