የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ቀይ ባሕር ነው ለምንግዜውም!
|
እውነትም ሚኒሊክ ምን ልበልክ …. #ምንይልክክ
ክክ |
ከኦሪት ጀምሮ ዛሬ እስካለንበት ዘመን ድረስ የኢትዮጵያ
ዳር ድንበር ቀይ ባሕር ነበር። ሙሴ እስራኤላዊያንን ይዞ ከግብፅ ወታደሮች ሲያመልጥ በኢትዮጵያ ላይ ተረማምዶ፣
ባሕር አቋርጦ ነው ወደ ሲና ተራራ የዘለቀው፣ ያ ባህርም ቀይ ባህር ነበር። ክርስትናን ወደ ኢትዮጵያ ይዘው የመጡት
ከሳቴ ብርሃንም ቀይ ባህርን አቋርጠው ነው ሃይማኖት የሰበኩት። አብርሃ ወአፅብሃ ደቡብ የመንን ያስገበሩት
የኢትዮጵያን ባሕር አልፈው ነው። ነቢዩ መሃመድ ተከታዮቹን ወደ ኢትዮጵያ ሲልክ አቋርጠው የመጡት ቀይ ባህርን ነው።
የትግራዩ ንጉሥ ንጉሴን ጨምሮ አፄ ዮሃንስ የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ቀይ ባህር መሆኑን ነው ያስተማሩን። ጀግናው አሉላ አባ ነጋ ፈረሱን የቀይ ባሕር ውኃ እንዳጠጣው ጠላቱንም ቀይ ባሕር እንደጨመረው ነው የምናውቅ አፄ
ቴዎድሮስ የአገሬ አፈር በነጭ ወራሪ አይሄድም ብለው ፈረንጆቹ እግራቸውን ሳይቀር ምፅዋ አፋፍ ላይ በቀይ ባሕር ውሃ
ታጥበው መሄዳቸውን ነው ታሪክ የሚነግረን አፄ ሚንሊክ ከአውሮፓውያን ጋር ባደረጉት ውል የኢትዮጵያ ድንበር ቀይ
ባሕር መሆኑን ታሪካዊ ማስረጃዎች አሉን። ከዚያ በኋላ ያለውን መዘርዘር አያሻም። እንኳንስ ቀይ ባሕር ከባህሩ ማዶ
ያሉት የሃኒሽ ደሴቶችም የኢትዮጵያ እንጂ የማንም ሆነው አያውቁም።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ