ሰኞ 24 ኦክቶበር 2016

የደብረ ዳሞ የገመድ መንገድ

እንደዚህ እንግዶች እያስተናገዱ ከ1400 ዓመታት በላይ አስቆጥረዋል፡፡ 

ጠመዝማዛው አቧራማ መንገድ አንድ ሦስት ቦታዎች ላይ ቆሎ ነጋዴዎች የመሠሉን ሰዎች አስቆሙን፡፡ ከጎናቸው ወርቃማ ጥላ የያዙ ሰዎች አሉ፡፡ በጥግ በኩል የተቀመጠ የጉዞ ባልደረባዬ ዝርዝር ካለህ የሁለት ብር ቆሎ ግዛልኝ፡አለኝ፡፡ የተባለውን ብር አውጥቼ ልከፍል ስል በነፃ ነው ተባልኩ፡፡ መኪናው ውስጥ ላለነው ሁሉ ቆሎ ታደለን፡፡ ጠላም መጣልን፡፡ እንግዶቻቸው እንደሆንን የነገሩን አስተናጋጆች በየዓመቱ ለሦስት ቀናት በዚህ መልኩ ይቀበላሉ፤ የአቡነ አረጋዊ እንግዶች ናችሁ በማለት፡፡

እንደዚህ እንግዶች እያስተናገዱ ከ1400 ዓመታት በላይ አስቆጥረዋል፡፡ ከሮም ከመጡት ዘጠኝ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አቡነ አረጋዊ፤ በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር የሚገኘውን የደብረዳሞ ገዳም የገደሙት የዛሬ 1469 ዓመት ነው፡፡ ይህን ገዳም ባለፈው ሳምንት ስንጎበኝ የገዳሙ መነኮሳት፤ ለምረቃው የወቅቱ ንጉሥ አፄ ገብረመስቀል እና ማህሌታይ ያሬድ እንደተገኙ ነግረውናል፡፡
በውስጡ የማርያም፣ የተክለሃይማኖት፣ የማትያስና አቡነ አረጋዊ አብያተ ክርስትያን የያዘው የደብረ ዳሞ ገዳም፤ በሀገሪቱ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ነው፡፡ በዘመናት የኢትዮጵያ የጦርነት ታሪክ አንዳችም አይነት ጉዳይ አልደረሰበትም፡፡ ከሌሎች መሠል ገዳማት ልዩ የሚያደርገውም ይኼና በገመድ መወጣጫ መወጣቱ ነው፡፡
ገመዱ
ሦስት አይነት ገመድ አይቻለሁ፡፡ የመጀመርያው ብዙ ሰው እየተሳበ ወደ ላይ የሚወጣበት እና እየተምዘገዘገ ወደ ታች የሚወርድበት ነው፡ በዚህ የገመድ መንገድ አብዛኛው የደብረ ዳሞ ወጪ ይጠቀምበታል፡፡ በሁለተኛው መንገድ፤ መንጠላጠሉ ይቅርብኝ ያለ ከወገቡ ታስሮ ከላይ በሚጎትቱት ሰዎች፣ ከጉድጓድ የውሃ ባልዲ እንደሚወጣው የሚወጣበት ነው፡፡ ሦስተኛው የእቃ መጫኛ ገመድ ነው፡፡ ገመዶቹ የተሰሩት አቡነ አረጋዊ መጀመርያ ደብረዳሞ ላይ ሲወጡ ዘንዶ በመጓጓዣነት ተጠቅመው የወጡትን በማገናዘብ ነው፡፡
ገመዱ ከጠንካራ የበሬ ቆዳ ይሰራል፡፡ ስምንት ሳንቲሜትር ዙሪያ እና አስር ሜትር ያህል ርዝመት ይኖረዋል፡፡ ከአምባው ጫፍ በታኮ ታስሯል፡፡ ሥሩ ደግሞ የ”ሀ” ቅርፅ አለው፡፡ በአንድ ጊዜ ወደ ላይ በአማካይ ስድስት፣ ወደ ታችም ስድስት ሰዎች ያስተናግዳል፡፡ ለመውጣትና ለመውረድ በሚደረግ ጥረት “ወጥቼ ጫፍ ደረስኩ” ከተባለ በኋላ ከላይ በሚመጡ የገመድ መንገደኞች እንደገና ወደ ታች መናድም አለ፤ አንዱን ካህንም የገጠማቸው ይኸው ነው፡፡ የገመዱን ሁለት ሦስተኛ ከተንጠላጠሉ በኋላ በሚወርዱ ሰዎች ተገፍተው መሬት መውረድ የግድ ሆኖባቸዋል፡፡ መወጣጫውን ዘመናዊ ለማድረግ በራስ መንገሻ ስዩም የተደረገው ጥረት ቅርስነቱን ያጠፋል በሚል እንደቀረ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡
ቅርስ ጥበቃ 1500 ዓመት ሊያስቆጥሩ 31 ዓመታት ብቻ የቀሯቸው የገዳሙ ቅርሶች አልተሰባሰቡም፡ ከአካባቢው መሬት የበለጠ ከፍታ ያለው አምባ (Plateau) ውበት ቢኖረውም የተፈጥሮ ፀጋው ተገፎ በመራቆት የአረንጓዴ ያለህ ያሰኛል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች ቢኖሩትም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አምባው ግርጌ ድረስ መጓዝ አስቸጋሪ ነበር፡፡
አሁን ግን ከ1.2 ሚሊዬን ብር በሚበልጥ ወጪ በሶስት አቅጣጫ የመወጣጫ ደረጃዎች ተሰርተውለታል፡፡ ከዚህ በሚመጣጠን ወጪ የጥንታዊ ቅርሶች ቤተመዘክር በሥፍራው ለማቋቋምም ጥቅምት 12 ቀን 2004 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ ተጥሏል፡፡ አካባቢውን በመከለል እና ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አካባቢ የመፍጠር ቀጣይ እቅድ እንዳላቸው የገለፁልን የደብረ ዳሞ ልማት ኮሚቴ ፀሐፊ አቶ ተወልደብርሃን ታደሰ፤ ከመወጣጫው ሌላ የአካባቢን ንፅሕና ለመጠበቅ መፀዳጃ ቤት እና ለእርድ ቄራ መሠራቱን አሳይተውናል፡፡ አረንጓዴነትን ለመመለስ ዛፍ ይተከላል፡፡ የፀበል ማጠራቀሚያ ጋንም ተሰርቷል፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነውና የሆነው ሕዝብ በማስተባበር እንደሆነ ነው አቶ ተወልደብርሃን የገለፁት፡፡
ገዳሙና ሴቶች
የአቡነ አረጋዊ እናት ተከትለዋቸው መጥተው ነበር፡፡ ነገር ግን አምባው ላይ መውጣት እንደማይቻል ልጅየው ስለነገሯቸው ከግርጌ በመሆን ይፀልዩ ጀመር፡፡ ይህ ቦታ እስካሁንም በአቡነ አረጋዊ በእናት ተሰይሟል፡፡ አጠገቡም መውለድ ያቃታቸው እና ወገባቸውን የታመው ሰዎች ይድኑበታል ተብሎ የሚነገርለት ጉድጓድ አለ፡፡ የወንዶች ገዳም በመሆኑ ደብረዳሞ ሴቶች እንዲወጡ አይፈቀድም፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት የገዳሙን ይዞታ ለማየት አንዲት የውጭ ሀገር ዜጋ ወንድ ነኝ በማለት በገመዱ ለመንጠላጠል ያደረገችውን ሙከራ መነኮሳት ጠባቂዎች አክሽፈውባታል፡፡ ይሁንም እንጂ በየዓመቱ ጥቅምት 14 ለአቡነ አረጋዊ ንግሥ በርካታ ሺህ ሴቶች ይሄዳሉ፡፡ በገመዱ ወደ ላይ ባይወጡም ገመዱን ደባብሰው ፊታቸውን በማባበስ ፃድቁን ይማፀናሉ፡፡ የአዲግራት ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ይርጋለም ኪዳኔ፤ “ሴቶች በገመዱ እንደማይወጡ ባውቅም በዓሉን ለማክበር መጥቻለሁ፡፡ የገዳሙ ታሪካዊነት እና የገመድ መወጣጫው ከሌሎች ይለዩታል፡፡” ብለዋል፡ ምንም እንኳ ሴቶች አምባው ላይ መውጣት ባይችሉም ካሉት አራት አብያተ ክርስትያናት ትልቁ የቅድስት ድንግል ማርያም ነው፡፡
እንደ ወ/ሮ ይርጋዓለም ከአዲግራት የመጣው ቻይናዊ ጎብኚ፤ ብዙ ሕዝብ ስላለ በገመዱ ተስቤ መውጣት አልቻልኩም፤ ሌላ ጊዜ መጥቼ እሞክራለሁ ብሏል፡፡ የአዲስ አበባው ፋሲል ኃይለማርያም ሞክሮ አቅቶታል፡፡ ቤልጅየማውያኑ ታታ ኩን እና ያዕቆብ ስሚዝ ገመዱን በአንድ ጊዜ በሚጠቀሙት ሰዎች ብዛት የተነሳ ፍርሀት አድሮባቸው ፈርተው እንደነበር ቢገልፁም በዚሁ ገመድ እየተሳቡ ደብረዳሞ አናት ላይ ደርሰዋል፤ በዚህ እና በአየሩ ፀባይ እንዲሁም በሕዝቡ መስተንግዶ መርካታቸውንም ነግረውኛል፡፡
የፀጥታ ጉዳይ ደብረዳሞ የወንዶች ገዳም ከኤርትራ ድንበር 5 ኪሎ ሜትር ይርቃል፡፡ ከዛሬ አስር አመት በፊት በነበረው ጦርነት አካባቢው የጦር ቀጠና የነበረ ሲሆን የሚመጣው ሰው ቁጥር ቢቀንስም ሰው አልቀረም ንግሡም አልተስተጓጎለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ድንበር ጠባቂ ከሆኑ ወታደሮች አንዱ የሆነው ወታደር እሱባለው ሞላ፤ ድንበር በመሆኑ የጎብኚ ቁጥር ይቀንሳል ብለው የሚገምቱ ሰዎች ስለመኖራቸው አንስቼበት፤ ጦሩ የተሟላ ጠንካራ ፍተሻ እንደሚያደርግ ነግሮኝ “የቱሪስት ፅህፈት ቤቶች ሊቀንስ ይችላል ቢሉም የጎብኚ ቁጥር አልቀነሰም፤ ምዕመናንና ሌሎች ጎብኚዎችም በድንበርነቱ የፀጥታ ችግር አላጋጠማቸውም ብሎኛል፡፡ ባለፈው ጥቅምት 14 ቀን 2004 ዓ.ም በርካታ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች የነበሩ ሲሆን፤ የቤልጂየም ተወላጁ ታታ ኩን ከፀጥታ ጉዳይ ጋር በተገናኘ ሲናገር “የኤርትራ ድንበር በመሆኑ አልፈራሁም፤ አንተ ፈራህ እንዴ” በማለት መልሶ ጠይቆኛል፡፡ ባለፉት 50 ዓመታት በተደጋጋሚ ደብረዳሞ ለንግስ የሚሄዱት አዛውንቱ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ አቶ ፀጋዬ በርኼ፤ ቁጥሩ ቢቀንስም በጦርነት ጊዜም ምዕመኑ ወደ ደብረዳሞ ሰው ይኼድ እንደነበረና በተወሰነ አቅጣጫ “በዚህ ሂዱ” ይባል እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ቀብር
በደብረ ዳሞ ገዳም ለአካባቢው ነዋሪዎችና በኑዛዜ ለሚቀበሩ 150 የመቃብር ጉድጓድ አለ፡ ይኼ ሲሞላ ሥጋ የረገፈበት አፅም ወደ ውስጥ ይገፋል፡ለበርካታ መቶ አመታት ለ በዚህ ቢቀጥልም የመቃብር ስፍራው በአፅም አለመሙላቱ ሁሌም እንደሚገርማቸው አንድ የአካባቢው ጎልማሳ ነግረውኛል፡፡
በአካባቢው ክርስትያኖች ሰው ሲሞት ቀብር ለመሸኘት ከሌላው የኢትዮጵያ አካባቢ የተለየ ሥርአት አለ፡፡ በመቀሌ ተመሳሳይ ስርዓት አይቻለሁ፡፡ ጉልላት መሠል ዣንጥላዎች የያዙ አምስት ስድስት ወጣቶች በረዥም ዘንግ ከፍ አርገው ይጓዛሉ፡ጥና የያዙ ካህናት ይከተሏቸዋል፡፡ ጥሩንባ ወይም እንቢልታ የሚነፋ ሰው ይቀጥላል፡፡ ከሱ ቀጥሎ የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ አድርገው የያዙ ሌሎች ወጣቶች ይሰለፋሉ፡፡ ከዚያ ወንዶች በመጨረሻም ሴቶች ተሰልፈው ሟችን “በደማቁ” ይሸኛሉ፡፡ የመቀሌው ቀብር ከጧቱ አንድ ሰዓት የተከናወነ ነበር፡፡
የገዳሙ መነኮሳት እና ልማት
ሃምሳ የሚሆኑት መነኮሳት መደበኛ ቀለብ ንፍኖ እና እንጀራ ነው፡፡ የገዳሙ አምባ ስፋት በግምት አስራሁለት የእግር ኳስ ሜዳ ቢሆንም አንዳችም የእርሻ እንቅስቃሴ የለም፡፡ የውሃ እጥረት ቢኖር እንኳ በዝናብ ውሃ በዓመት ቢያንስ አንዴ ማምረት ይቻላል፡ለቤተክህነትም ሆነ ለመንግስት ግብር ማስገባት አይጠበቅበትም፡፡ ከስዕለት እና ከስጦታ የራሱ ገቢ ያለው “ሀብታም ገዳም” ነው፡ ከፀሎት በሚተርፋቸው ጊዜ መነኮሳቱ እርሻ እና ሽመናን በመሳሰሉ ሥራዎች ቢሰማሩ ገዳሙ የተሻለ “ሀብታም” በመሆን ለሌሎችም ይተርፋል፡፡ የገዳሙ አስተዳዳሪ መምህር ብርሃነ መስቀል ኪዳነ ማርያምን ስለዚሁ ጠይቄአቸው “ቦታው ድንጋያማ ነው ተክለን አላበቀለም፣ ቢሆንም ቀሌምጦስ (ባህርዛፍ)ን ጨምሮ እንተክላለን ይደርቃል፡፡ ራሴ 30 ተክዬ አራት ብቻ ይዘዋል፤ እነሱም አያስተማምኑም” ያሉት መምህሩ፤ 70 የሚሆኑት መነኮሳት ቆብ እና አስኬማ መስራትን ጨምሮ ሁለት ሦስት ሥራ ስለሚሰሩ ጊዜ እንደሌላቸውም ይናገራሉ፡፡ጠመዝማዛው አቧራማ መንገድ አንድ ሦስት ቦታዎች ላይ ቆሎ ነጋዴዎች የመሠሉን ሰዎች አስቆሙን፡፡ ከጎናቸው ወርቃማ ጥላ የያዙ ሰዎች አሉ፡፡ በጥግ በኩል የተቀመጠ የጉዞ ባልደረባዬ ዝርዝር ካለህ የሁለት ብር ቆሎ ግዛልኝ፡አለኝ፡፡ የተባለውን ብር አውጥቼ ልከፍል ስል በነፃ ነው ተባልኩ፡፡ መኪናው ውስጥ ላለነው ሁሉ ቆሎ ታደለን፡፡ ጠላም መጣልን፡፡ እንግዶቻቸው እንደሆንን የነገሩን አስተናጋጆች በየዓመቱ ለሦስት ቀናት በዚህ መልኩ ይቀበላሉ፤ የአቡነ አረጋዊ እንግዶች ናችሁ በማለት፡፡
እንደዚህ እንግዶች እያስተናገዱ ከ1400 ዓመታት በላይ አስቆጥረዋል፡፡ ከሮም ከመጡት ዘጠኝ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አቡነ አረጋዊ፤ በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር የሚገኘውን የደብረዳሞ ገዳም የገደሙት የዛሬ 1469 ዓመት ነው፡፡ ይህን ገዳም ባለፈው ሳምንት ስንጎበኝ የገዳሙ መነኮሳት፤ ለምረቃው የወቅቱ ንጉሥ አፄ ገብረመስቀል እና ማህሌታይ ያሬድ እንደተገኙ ነግረውናል፡፡
በውስጡ የማርያም፣ የተክለሃይማኖት፣ የማትያስና አቡነ አረጋዊ አብያተ ክርስትያን የያዘው የደብረ ዳሞ ገዳም፤ በሀገሪቱ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ነው፡፡ በዘመናት የኢትዮጵያ የጦርነት ታሪክ አንዳችም አይነት ጉዳይ አልደረሰበትም፡፡ ከሌሎች መሠል ገዳማት ልዩ የሚያደርገውም ይኼና በገመድ መወጣጫ መወጣቱ ነው፡፡
ገመዱ
ሦስት አይነት ገመድ አይቻለሁ፡፡ የመጀመርያው ብዙ ሰው እየተሳበ ወደ ላይ የሚወጣበት እና እየተምዘገዘገ ወደ ታች የሚወርድበት ነው፡ በዚህ የገመድ መንገድ አብዛኛው የደብረ ዳሞ ወጪ ይጠቀምበታል፡፡ በሁለተኛው መንገድ፤ መንጠላጠሉ ይቅርብኝ ያለ ከወገቡ ታስሮ ከላይ በሚጎትቱት ሰዎች፣ ከጉድጓድ የውሃ ባልዲ እንደሚወጣው የሚወጣበት ነው፡፡ ሦስተኛው የእቃ መጫኛ ገመድ ነው፡፡ ገመዶቹ የተሰሩት አቡነ አረጋዊ መጀመርያ ደብረዳሞ ላይ ሲወጡ ዘንዶ በመጓጓዣነት ተጠቅመው የወጡትን በማገናዘብ ነው፡፡
ገመዱ ከጠንካራ የበሬ ቆዳ ይሰራል፡፡ ስምንት ሳንቲሜትር ዙሪያ እና አስር ሜትር ያህል ርዝመት ይኖረዋል፡፡ ከአምባው ጫፍ በታኮ ታስሯል፡፡ ሥሩ ደግሞ የ”ሀ” ቅርፅ አለው፡፡ በአንድ ጊዜ ወደ ላይ በአማካይ ስድስት፣ ወደ ታችም ስድስት ሰዎች ያስተናግዳል፡፡ ለመውጣትና ለመውረድ በሚደረግ ጥረት “ወጥቼ ጫፍ ደረስኩ” ከተባለ በኋላ ከላይ በሚመጡ የገመድ መንገደኞች እንደገና ወደ ታች መናድም አለ፤ አንዱን ካህንም የገጠማቸው ይኸው ነው፡፡ የገመዱን ሁለት ሦስተኛ ከተንጠላጠሉ በኋላ በሚወርዱ ሰዎች ተገፍተው መሬት መውረድ የግድ ሆኖባቸዋል፡፡ መወጣጫውን ዘመናዊ ለማድረግ በራስ መንገሻ ስዩም የተደረገው ጥረት ቅርስነቱን ያጠፋል በሚል እንደቀረ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡
ቅርስ ጥበቃ
1500 ዓመት ሊያስቆጥሩ 31 ዓመታት ብቻ የቀሯቸው የገዳሙ ቅርሶች አልተሰባሰቡም፡ ከአካባቢው መሬት የበለጠ ከፍታ ያለው አምባ (Plateau) ውበት ቢኖረውም የተፈጥሮ ፀጋው ተገፎ በመራቆት የአረንጓዴ ያለህ ያሰኛል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች ቢኖሩትም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አምባው ግርጌ ድረስ መጓዝ አስቸጋሪ ነበር፡፡
አሁን ግን ከ1.2 ሚሊዬን ብር በሚበልጥ ወጪ በሶስት አቅጣጫ የመወጣጫ ደረጃዎች ተሰርተውለታል፡፡ ከዚህ በሚመጣጠን ወጪ የጥንታዊ ቅርሶች ቤተመዘክር በሥፍራው ለማቋቋምም ጥቅምት 12 ቀን 2004 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ ተጥሏል፡፡ አካባቢውን በመከለል እና ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አካባቢ የመፍጠር ቀጣይ እቅድ እንዳላቸው የገለፁልን የደብረ ዳሞ ልማት ኮሚቴ ፀሐፊ አቶ ተወልደብርሃን ታደሰ፤ ከመወጣጫው ሌላ የአካባቢን ንፅሕና ለመጠበቅ መፀዳጃ ቤት እና ለእርድ ቄራ መሠራቱን አሳይተውናል፡፡ አረንጓዴነትን ለመመለስ ዛፍ ይተከላል፡፡ የፀበል ማጠራቀሚያ ጋንም ተሰርቷል፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነውና የሆነው ሕዝብ በማስተባበር እንደሆነ ነው አቶ ተወልደብርሃን የገለፁት፡፡
ገዳሙና ሴቶች
የአቡነ አረጋዊ እናት ተከትለዋቸው መጥተው ነበር፡፡ ነገር ግን አምባው ላይ መውጣት እንደማይቻል ልጅየው ስለነገሯቸው ከግርጌ በመሆን ይፀልዩ ጀመር፡፡ ይህ ቦታ እስካሁንም በአቡነ አረጋዊ በእናት ተሰይሟል፡፡ አጠገቡም መውለድ ያቃታቸው እና ወገባቸውን የታመው ሰዎች ይድኑበታል ተብሎ የሚነገርለት ጉድጓድ አለ፡፡ የወንዶች ገዳም በመሆኑ ደብረዳሞ ሴቶች እንዲወጡ አይፈቀድም፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት የገዳሙን ይዞታ ለማየት አንዲት የውጭ ሀገር ዜጋ ወንድ ነኝ በማለት በገመዱ ለመንጠላጠል ያደረገችውን ሙከራ መነኮሳት ጠባቂዎች አክሽፈውባታል፡፡ ይሁንም እንጂ በየዓመቱ ጥቅምት 14 ለአቡነ አረጋዊ ንግሥ በርካታ ሺህ ሴቶች ይሄዳሉ፡፡ በገመዱ ወደ ላይ ባይወጡም ገመዱን ደባብሰው ፊታቸውን በማባበስ ፃድቁን ይማፀናሉ፡፡ የአዲግራት ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ይርጋለም ኪዳኔ፤ “ሴቶች በገመዱ እንደማይወጡ ባውቅም በዓሉን ለማክበር መጥቻለሁ፡፡ የገዳሙ ታሪካዊነት እና የገመድ መወጣጫው ከሌሎች ይለዩታል፡፡” ብለዋል፡ ምንም እንኳ ሴቶች አምባው ላይ መውጣት ባይችሉም ካሉት አራት አብያተ ክርስትያናት ትልቁ የቅድስት ድንግል ማርያም ነው፡፡
እንደ ወ/ሮ ይርጋዓለም ከአዲግራት የመጣው ቻይናዊ ጎብኚ፤ ብዙ ሕዝብ ስላለ በገመዱ ተስቤ መውጣት አልቻልኩም፤ ሌላ ጊዜ መጥቼ እሞክራለሁ ብሏል፡፡ የአዲስ አበባው ፋሲል ኃይለማርያም ሞክሮ አቅቶታል፡፡ ቤልጅየማውያኑ ታታ ኩን እና ያዕቆብ ስሚዝ ገመዱን በአንድ ጊዜ በሚጠቀሙት ሰዎች ብዛት የተነሳ ፍርሀት አድሮባቸው ፈርተው እንደነበር ቢገልፁም በዚሁ ገመድ እየተሳቡ ደብረዳሞ አናት ላይ ደርሰዋል፤ በዚህ እና በአየሩ ፀባይ እንዲሁም በሕዝቡ መስተንግዶ መርካታቸውንም ነግረውኛል፡፡
የፀጥታ ጉዳይ
ደብረዳሞ የወንዶች ገዳም ከኤርትራ ድንበር 5 ኪሎ ሜትር ይርቃል፡፡ ከዛሬ አስር አመት በፊት በነበረው ጦርነት አካባቢው የጦር ቀጠና የነበረ ሲሆን የሚመጣው ሰው ቁጥር ቢቀንስም ሰው አልቀረም ንግሡም አልተስተጓጎለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ድንበር ጠባቂ ከሆኑ ወታደሮች አንዱ የሆነው ወታደር እሱባለው ሞላ፤ ድንበር በመሆኑ የጎብኚ ቁጥር ይቀንሳል ብለው የሚገምቱ ሰዎች ስለመኖራቸው አንስቼበት፤ ጦሩ የተሟላ ጠንካራ ፍተሻ እንደሚያደርግ ነግሮኝ “የቱሪስት ፅህፈት ቤቶች ሊቀንስ ይችላል ቢሉም የጎብኚ ቁጥር አልቀነሰም፤ ምዕመናንና ሌሎች ጎብኚዎችም በድንበርነቱ የፀጥታ ችግር አላጋጠማቸውም ብሎኛል፡፡ ባለፈው ጥቅምት 14 ቀን 2004 ዓ.ም በርካታ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች የነበሩ ሲሆን፤ የቤልጂየም ተወላጁ ታታ ኩን ከፀጥታ ጉዳይ ጋር በተገናኘ ሲናገር “የኤርትራ ድንበር በመሆኑ አልፈራሁም፤ አንተ ፈራህ እንዴ” በማለት መልሶ ጠይቆኛል፡፡ ባለፉት 50 ዓመታት በተደጋጋሚ ደብረዳሞ ለንግስ የሚሄዱት አዛውንቱ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ አቶ ፀጋዬ በርኼ፤ ቁጥሩ ቢቀንስም በጦርነት ጊዜም ምዕመኑ ወደ ደብረዳሞ ሰው ይኼድ እንደነበረና በተወሰነ አቅጣጫ “በዚህ ሂዱ” ይባል እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ሃምሳ የሚሆኑት መነኮሳት መደበኛ ቀለብ ንፍኖ እና እንጀራ ነው፡፡ የገዳሙ አምባ ስፋት በግምት አስራሁለት የእግር ኳስ ሜዳ ቢሆንም አንዳችም የእርሻ እንቅስቃሴ የለም፡፡ የውሃ እጥረት ቢኖር እንኳ በዝናብ ውሃ በዓመት ቢያንስ አንዴ ማምረት ይቻላል፡ለቤተክህነትም ሆነ ለመንግስት ግብር ማስገባት አይጠበቅበትም፡፡ ከስዕለት እና ከስጦታ የራሱ ገቢ ያለው “ሀብታም ገዳም” ነው፡ ከፀሎት በሚተርፋቸው ጊዜ መነኮሳቱ እርሻ እና ሽመናን በመሳሰሉ ሥራዎች ቢሰማሩ ገዳሙ የተሻለ “ሀብታም” በመሆን ለሌሎችም ይተርፋል፡፡ የገዳሙ አስተዳዳሪ መምህር ብርሃነ መስቀል ኪዳነ ማርያምን ስለዚሁ ጠይቄአቸው “ቦታው ድንጋያማ ነው ተክለን አላበቀለም፣ ቢሆንም ቀሌምጦስ (ባህርዛፍ)ን ጨምሮ እንተክላለን ይደርቃል፡፡ ራሴ 30 ተክዬ አራት ብቻ ይዘዋል፤ እነሱም አያስተማምኑም” ያሉት መምህሩ፤ 70 የሚሆኑት መነኮሳት ቆብ እና አስኬማ መስራትን ጨምሮ ሁለት ሦስት ሥራ ስለሚሰሩ ጊዜ እንደሌላቸውም ይናገራሉ፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ