2016 ኖቬምበር 18, ዓርብ

ጥበብ #Yemane_Abadi

በነ ሽብሩ ስንሸበር +Yemane Abadi 
እንደኔ ግንዛቤ ጥበብን እንደተሸበበች በቅሎ በአንድ አቅጣጫ ብቻ መመልከት ሙሉ አይመስለኝም፤ እንደ ኢትዮጵያዊያን የአንድምታ ትርጓሜ በተለያየ አቅጣጫና ደረጃ ገጽታዋ ሊታይና ሊነገር ይገባዋል፡- በቻል አራት ዓይና መኾንን ትፈልጋለች፡፡ ለእኔ በጥቅል የተረዳሁት የመሰለኝ የጥበብ ምንነት ልግለጽ፤ ለእኔ ጥበብ በተዋህዶ የምትሠልስ ናት፤ ማለት የጥበብ ትርጉምየእውነት፣ የዕውቀትና የመልካምነት ተዋህዶ (ቅኔ)› ነው፤ አንድም በኢትዮጵያውኛ እንግለጻት ካልንጥበብ ማለት ቅኔ ናት› (ግጥም አላልኩም) ካሠራር ብልሃት አንጻር ካየናትምጥበብ ማለት ፊደል ናት አንድም በመንፈሳዊ ዕይታ ከተመለከትናት ጥበብ እግዚአብሔርን (ሥላሴ) ወይም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥርነት ፈክራ ታመሠጥራለች፡፡ እንደ ጠቢቡ ሰለሞን ከሆነጥበብ ሰባት አዕማዳት ያሏት ቤትነች፡፡ ስለዚህ ጥበብን በተለያየ ዕይታና አተረጓገም መቃኘት ይገባል፤ ግን መሠረታዊ ትርጓሜዋን መልቀቅ የለባትም፤ ያንኑ ማምጠቅ ወይም መወሰን ወይም የትኩረት አቅጣጫዋ መወሰን ወይም የአስተውሎት ልዩነት ነው ልዩነቱን የሚፈጥረው፤ አንድም የትርጓሜው ልዩነት የሚፈጠረው ከምትታይበት የአንግል መለያየት የተነሣ ይሆናል፤ ለማንኛው እነዚህን አንድማታዊ ትርጓሜዎች እንቃኛቸው፡- ቅኔነቷን እየፈታን፤ የላይ ቤትና የታች ቤት ምሥጢራዊ ትርጓሜዋን እየለየን እንያት፡፡
በመሠረትነት ጥበብ የእውነት፣ የዕውቀትና የመልካምነት ተዋህዶ ሥሪት ናት፡፡ ጥበብን ልዩ ተወዳጅ ያደረጋትም እነዚህን ነገሮች አወህዳ የያዘች መሆኗ ነው፡፡ ከእነሱም እውነት መሠረት፣ ዕውቀት ግድግዳና ጣሪያ፣ መልካምነት ደግሞ ልስንና ክዳን በመሆን የተዋበችውን የጥበብ ቤት ሠርተዋታል፡፡ ይህች ቤት ናት እንግዲህ ስንቶችን በፍቅር እያከነፈች ስባ ካስገባች በኋላ ነፍሳቸውን አሳልፈው እንዲሰጧት የምታደርገው፤ ከመሠረት አሠራሯና ንድፏ እስከ አመራረግ፣ አለሣሰን፣ አከዳደንና አቀባብ ውበቷ እየተደነቁ በፍቅር ከንፈው የቀሩላት፣ መኖሪያ እሥር ቤታቸው ያደረጓት ለዚያ ነው፡- እንዴት ብለው ይልቀቋት ትንሽ የምትመስል የዓለምን ምንነት ማወቂያና መገምገሚያ መነጽር ያላት አስደናቂ ቤት ሆና!፡፡ ከእነዚህ ከሦስት አስፈላጊ ነገሮች አንዷ ከተለየች ሦስቱም አይነሩም፤ አንዱ ያለ ሌላው ህልውና የላቸውም ምክንያቱም ጥበብን ወይም የጥበብ ቤትን ማስገኘት የቻሉት በመያያዝ ስለሆነ አይነጣጠሉም፡፡ ይህም ማለት እውነት ያለ ዕውቀት መታወቅ አትችልም፤ እውነትነት የሌለው ዕውቀትም ትርጉም የለውም፤ ያለ ዕውቀትና ያለ እውነት መልካምነት አይገለፅም፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሦስት የጥበብ መሠሪያዎች በአንድነትና በሡልስነት ተዋህደው ጥበብን ያከበሩ ናቸው፡፡
ጥበብ ደግሞ የምትሠራው በብልሃት ነው፤ የብልሆችም መዋያና ማደሪያም ትሆናለች፡፡ የሰው ልጅ ደግሞ በተፈጥሯዊ ባህርዩ ብልሃትን የታደለ ፍጡር ስለሆነ ኹሉም ሰው ጠቢብ (ፈላስፋ) ነው ይባላል፡፡ አነጋገሩ እውነታነት አለው፤ አበውምአእምሮ እስካለ ድረስ ቅኔ ሊጠፋ አይችልምየሚሉት ለዚያ ነው፤ ግን ጥንቃቄንም ይጠይቃል ምክንያቱም ኮከብ እምኮከብ ይኄይስ ክብሩ፡- ከአንዱ ኮከብ ክብር የአንዱ ኮከብ ክብር ይበልጣልእንዳለው .ጳውሎስ፤ አንድ ጣት ከሌላው ጣት ሲነጻጸር እንደሚበላለጠው፤ የጠቢባኑም ደረጃና ብልሃት ተነጻጽሮ የተሻለው ጥበብ የበለጠ ሳቢነትንና ተደናቂነት ያገኛል፡፡ እንዲሁም የጥበብ ቤት የምትሠራው በዘመን ሂደት በጠቢባኑ ቅብብሎሽና ትብብር፣ ወይም መናበብ ነው፡- የጥበብ ቤት የስንት አብሰልስሎት ሥራ ናት፤ ስንትና ስንት የአእምሮ ማገዶ ፈጅታለች፡፡ ስለዚህ በሚገኙበት የዘመን ማዕዘንና ዕይታ ድንጋዩን፣ ዕንጨቱን፣ ሣሩን፣ ማገሩን፣ ጭቃውን፣ ቀለሙንና የመሳሰሉት በማቀበልና በማስተካከል ባደረጉት አስተዋፅኦ፣ መተራረምና ማስተካከል ነው ጥበብ በቤትነት የተሠራችው፡- በተላይ ደግሞ በተመረጡ ባለሙያዎች፡፡ ስለዚህ አሁን የምትገኘው ጥበብ ጠቢባን ለብዙ ዘመናት ለእውነት፣ ዕውቀትና መልካምነት ግንባታ የአእምሮ ጉልበታቸውን የጨረሱባት ናት፡፡ በሌላ አባባል የጠቢባነ-ጠቢባኑ እየተከራከሩ፣ እየተመካከሩና እየተራረሙ የእውነት ዓለትን አጥብቀው (አንጠርው) በመመሥረት፣ በዕውቀት መሣሪያነት አስልተውና አስተካክለው በመሥራት በመልካምነት እሴት አስውበውና አክብረው እኛ አለንበት ዘመን ጋር አድርሰዋታል፡፡ ለዚያም ነው
የሚጥሩ ሰዎች ለዕውቀት የታጠቁ፣
በጣም ክቡር ናቸው እንደ አልመዝ እንደ ዕንቁ፡፡የተባለላቸው፡፡
አንድምጥበብ ማለት የተዋህዶ ቅኔ ነችባልነው ትመሠጠራለች፡፡ ተዋህዶና ቅኔ የኢትዮጵያ ሊቃውንትን ለዘመናት ያስጠበቡ፣ ገና ዓለም በሥጋዊ ዓይኑ በአግባቡ ያላያቸው ድንቅ ጥበባት ናቸው፤ የሚለያዩት በስማቸው እንጂ በምሥጢር በአንድነት ይገናዘባሉ፡፡ ለዚያም ነው ጥበብ የተዋህዶ ቅኔ የተባለችው፤ ዕንቆቅልሻዊ ተፈጥሮ አላት፡፡ አንድም ጥበብ ማለት አእምሯችን መጥቆ ውስብስቡን፣ የማይታየውንና ረቂቃዊን ዓለም በሚታየው የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማነጻጸርና በማዋሃድ እየለየ የሚፈታባት የኹለት ኑባሬያት ተዋህዶ የሆነች ቅኔ ወይም የሰምና የወርቅ ምሥጢራዊ የተራቆ ትርጉምን ያቀፈች ድንቅ ነገር ነች፡፡፡ በዚህም አዕምሯችን የማይታየውንና መልስ ያልተገኘለትን ስውርና ውስብስብ ክስተት መልስ ባለውና ግልፅ ሆኖ በሚታወቀው እያነጻጸረና የሚታወቀውን ተጠቅሞ ውስብስቡን እየፈታ፤ ያልተገለጠውን ደግሞምንድን? ለምን? እንዴት?› በሚሉ ጥያቄዎች እያበጠረ ሥውሩን ገልጾ የሚለይባት ማጉሊያ መሣሪያው ናት፡- ጥበብ፡፡

2016 ኦክቶበር 27, ሐሙስ



Wolkait

The Wolkait issue isn’t an identity question rather a propaganda ploy designed to bring discord between the people of Amhara and Tigray

Debretsion Gebremichael (PhD), Minister of Communication and Information Technology and coordinator of finance and economic cluster with the rank of deputy prime minister.
Dr. Debretsion Gebremichael, Minister of Communication and Information Technology and coordinator of finance and economic cluster with the rank of deputy prime minister, said the issue of Wolkait isn’t an identity question.
During the biannual GTPII performance meeting with employees and administrative staff of EthioTelecom, Dr. Debretsion commented “If the wolkait issue was a question of identity, it would have been raised by the people of Wolkait themselves in Wolkait, not in Gondar”
Debretsion also said that the people of Kimant has raised an identity question themselves and that was handled as per the constitutional procedure. The same goes for Wolkait.
“ethnicity is not something we created or strengthened. It was there all along history and the federalism was the only option for our country to continue intact” he added.
According to the deputy premier, the federalism answered the national question and brought stability for 25 years. If it was the problem we wouldn’t have lasted this long. He underlined that the Wolkait issue is a political propaganda ploy designed to bring discord between the people of Amhara and Tigray.
*
*
*
http://www.awrambatimes.com/?p=15208